አመራሩ የአስተሳሰብ አንድነትን እንዲሁም የወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴትን ማጠናከር አለበት

You are currently viewing አመራሩ የአስተሳሰብ አንድነትን እንዲሁም የወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴትን ማጠናከር አለበት
  • Post category:ፖለቲካ

‎AMN ህዳር 10/2018 ዓ.ም

‎አመራሩ የአስተሳሰብ አንድነትን እንዲሁም የወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴትን ማጠናከር እንዳለበት በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሞገስ ባልቻ ገለጹ።

‎የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት ሁለተኛ ዙር የከፍተኛና መካከለኛ የአመራር አባላት ስልጠና በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

‎በስልጠናው የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛና መካከለኛ አመራር አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

‎ስልጠናው “በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ ለሚቀጥሉት ስምንት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።

‎በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሞገስ ባልቻ በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት ገለጻ፤ አመራሩ የአስተሳሰብ አንድነትን እንዲሁም የወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴትን ማጠናከር ይገባዋል ብለዋል።

‎የስልጠናው ዓላማም በአመራሩ መካከል የበለጠ መቀራረብና የአስተሳሰብ አንድነትን መፍጠር እንዲሁም የወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴትን ማጎልበት መሆኑን ገልጸዋል።

‎በተጨማሪም አገልጋይና ሁለገብ የሆነ አመራር መፍጠር ከስልጠናው ዓላማዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡

‎ስልጠናው በተለያዩ ሀገራዊ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በማተኮር እንደሚሰጥም ተናግረዋል።

‎በዚህም ስልጠናው በመደመር መንግስት እይታ የግብርና፣ የገጠር፣ የመዋቅራዊ ትራንስፎርሜሽን ጉዞ፣ የኢንዱስትሪ እና የቱሪዝም ዘርፍ እመርታ እንዲሁም የከተማ ልማት በሚል ርዕሶች ላይ እንደሚያተኩር ገልጸዋል፡፡

‎ስልጠናው የአመራሩን እውቀት፣ ክህሎትና አቅም የሚገነባ መሆኑንም ተናግረዋል።

‎በስልጠናው ከሁለት ሺህ በላይ የፌዴራልና የከተማዋ ከፍተኛና መካከለኛ አመራር አባላት እንደሚሳተፉና ጎን ለጎንም የተግባርና የመስክ የልማት ስራ ጉብኝቶች እንደሚከናወኑ ተገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review