የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከማሌዥያዋ ከኳላ ላምፑር ከተማ ጋር የእህትማማችነት የትብብር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸዉን ገለጹ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የማሌዥያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም በተገኙበት ፤ በማሌዥያዋ ኳላ ላምፑር ከተማ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መካከል የእህትማማችነት የትብብር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል ሲሉ ገልጸዋል።