ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት በኢትዮጵያ የሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያደረጉትን የማሌዢያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂምን ወደ ሀገራቸው ሸኝተናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ቆይታ በሁለትዮሽ የጋራ አጀንዳዎች ላይ ውይይት የተካሄደበት እና በተለያዩ ዘርፎች ስምምነት የተደረሰበት ፍሬያማ ቆይታ ነበር ሲሉ ገልጸዋል፡፡