ኢጋድ የአየር ንብረት ለውጥ ያተኮሩ ዘገባዎችን የሚሸልምበት የሚዲያ አዋርድ በአዲስ አበባ ሊያካሂድ ነው

You are currently viewing ኢጋድ የአየር ንብረት ለውጥ ያተኮሩ ዘገባዎችን የሚሸልምበት የሚዲያ አዋርድ በአዲስ አበባ ሊያካሂድ ነው

‎AMN ህዳር 12/2018ዓ.ም

‎የ2025 የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት ( ኢጋድ) የሚዲያ አዋርድ ከህዳር 20 እስከ 21 በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለፀ ።

‎የሚዲያ አዋርዱን ተከትሎ የምስራቅ አፍሪካ ልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ ) የኢትዮጲያ ተወካይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል ።

‎ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የኢጋድ የኢትዮጲያ ተወካይ በፈረጆቹ 2023 የጀመረ መሆኑን ጠቅሰው፣

‎ሚዲያ አዋርዱ የዘንድሮውም ለአየር ንብረት ለውጥ የተወሰደውን እርምጃ እና ቀጣይ ትግበራን መሰረት ያደረገ ዘገባዎችን እንደሚያወዳድር ተመላክቷል።

‎ኢጋድ ከሚሰራባቸው የስራ ዘርፎች መካከል የአየር ንብረት ለውጥ አንዱ መሆኑን ያነሱት ተወካዩ ፣የአየር ንብረት ለውጥን ለመመከት የሚሰሩ ስራዎችን ለማበረታታት ያለመ መሆኑም ጠቁመዋል ።

‎የውድድር መርሀ ግብሩ ስምንት ዘርፎች ያሉት ሲሆን ህትመት ሚዲያ፣ፎቶግራፍ ጋዜጠኝነት ፣ሀገር በቀል ቋንቋዎች ፣ ቴሌቭዥኝ ፣ ራዲዮና ዲጅታል ሚዲያ የተሰሩ ዘገባዎችን ተጠቃሽ መሆናቸው ተመላክቷል።

‎የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ታደሰ በበኩላቸው ፣ኢትዮጲያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ጨምሮ በታዳሽ ሀይል ለቀጠናው ተሞክሮ የሚሆኑ ስራዎች እያከናወነች ትገኛለች ብለዋል።

‎በዚህም ሁለተኛውን አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ያካሄደችበትን መድረክ አስታውሰው ፣ ይህ ተግባሯ የኮፕ 32 ጉባኤንም ለማስተናገድ እንድትመረጥ አስችሏታል ብለዋል።

‌‎ለሚዲያ አዋርዱ በርከት ያሉ ጋዜጠኞች ከቀጠናው ወደ ኢትዮጲያ እንደሚመጡ ያነሱት አምባሳደር ነብያት ይህም የኢትዮጵያን ገፅታ ለሚያስተዋውቅ ትልቅ መድረክ በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

‎በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review