ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ 3ኛ ጨዋታ ሶማሊያን የገጠመችው ኢትዮጵያ 3ለ3 ተለያይታለች
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዳዊት ካሳው በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት ሁለት ግብ ሲያስቆጥር አቤኔዘር አለማየሁ ሌላኛውን ግብ ማስገኘት ችሏል።
አጥቂው ዳዊት ካሳው በውድድሩ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ ስድስት ከፍ አድርጓል።
ለሶማሊያ አብድራሺድ ኦማር ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ሲያሳርፍ ቢላል ዩሱፍ ሌላኛውን ግብ አስቆጥሯል።
ኢትዮጵያ ከሦስት ጨዋታ ሰባት ነጥብ ሰብስባለች።
በሸዋንግዛው ግርማ