ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፖሊስ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በራስ አቅም ያሠለጠናቸውን እጩ መኮንኖች አስመረቁ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፖሊስ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በራስ አቅም ያሠለጠናቸውን እጩ መኮንኖች አስመረቁ

AMN ህዳር 13/2018

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክትዛሬ ማለዳ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፖሊስ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በራስ አቅም ያሠለጠናቸውን እጩ መኮንኖች መርቀናል ብለዋል።

ተመራቂ መኮንኖች፣ ለዚህ ትልቅ ስኬት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፣ በስልጠና ያገኛችሁት ተጨማሪ አቅም ከማህበረሰቡ፣ ከሌሎችም የፀጥታ ተቋማትና የሙያ ባልደረቦቻችሁ ጋር በመቀናጀት የከተማችንን ሰላሞና ፀጥታ የምታፀኑበት እንደሚሆን እምነት አለኝ።

ውድ ተመራቂ መኮንኖች፤ ወደ ሥራ ስትሰማሩ ሙያችሁን በታማኝነት፣ በቅንነት፣ ለእውነት በመወገንና በአርቆ አሳቢነት በመመራት ሐቀኛ የሕዝብ አገልጋይነትን በብቃት እንድትወጡ አደራ እላለሁ።

የከተማ አስተዳደሩ ኮሌጁ በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ ለመሆን ለሰነቀው ራዕይ እንደ ሁልጊዜውም ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review