ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ፕሬዚደንት ጋር ተወያዩ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ፕሬዚደንት ጋር ተወያዩ

AMN-ህዳር 13/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ፕሬዚደንት ክሪስታሊና ጂኦርጂየቫ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት “በቡድን 20 ጉባኤ ጎን ለጎን ከIMF ፕሬዝደንት ክሪስታሊና ጂኦርጂየቫ ጋር በአለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያዎች ፣ በሀገራችን የኢኮኖሚ ሪፎርም እንዲሁም ዘላቂ እና አካታች እድገትን ለመደገፍ ትብብራችንን ለማጠናከር ስላሉ እድሎች ላይ ተወያይተናል” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለIMF የዘለቀ ግንኙነት ምስጋናቸውን አቅርበው የጋራ ትኩረቶችን ለመፈፀም መነሳታቸውንም ገልፀዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review