በአዲስ አበባ የተገነቡ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ገለጹ፡፡
15ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል ተካሂዷል፡፡
በፌስቲቫሉ ላይ በንግግር የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን መንግሰት ኣካል ጉዳተኞች እና መስማት ለተሳናቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ግምት ውስጥ በማስገባት የማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውን ተናግረዋል፡፡
ፌስቲቫሉ በየአመቱ መካሄዱ አካል ጉዳተኞች እና መስማት የተሳናቸው አቅም እና ችሎታ እንዳላቸው ያሳያል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፓራ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንት አቶ መዝገቡ አቢዩ በበኩላቸው ፌስቲቫሉ አካል ጉዳተኞች የሚችሉ መሆናቸውን ለማሳየት እና በህብረተሰቡ ውስጥ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ ለአካ ጉዳተኞች ተደራሽ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡
የፌስቲቫሉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነት እና ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን አመልክተዋል፡፡ ውድድሩ አካል ጉዳተኞች እንደሚችሉ ማሳይም ነው ብለዋል፡፡
”አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማህበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማህበራዊ እድገት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ውድድር ከሕዳር 13 እስከ ሕዳር 24/2018ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል፡፡
ሰለሞን በቀለ