ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከካፍ ፕሬዝደንት ከዶክተር ፓትሪስ ሞትሲፒ በአፍሪካ እግር ኳስ እና ኢትዮጵያ በእድገቱ ስለሚኖራት ሚና ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ለወጣቶች እድገት፣ የስፖርት መሠረተ ልማት ብሎም የአፍሪካን እግርኳስ በዓለም መድረክ ለማላቅ ከካፍ ጋር ስለሚኖረን ትብብር ተወያይተናል በማለትም አመላከተዋል።