AMN ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ/
25ኛው የሶፊ ማልት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጰያ በስኬት መጠናቀቁ የአዲስ አባባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
መነሻና መዳረሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ የተካሄደው 25ኛው የሶፈ ማልት ታላቁ ሩጫ ውድድር በስኬት መጠናቀቁን የአዲስ አባባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለኤ ኤም ኤን በላከው መግለጫ አሳውቋል

መምሪያው የውጭ ሀገር ዜጎች ፣ አምባሳደሮች ፣ ታዋቂ ሰዎች እና በርካታ ህዝብ የታደሙበት ከተማችን አዲስ አበባ ለ25ኛ ጊዜ ያስተናገደችው ሩጫ በስኬት ተጠናቋል ብሏል፡፡
ፖሊስ መምሪያው ፕሮግራሙ በአግባቡ እንዲከናወን የፀጥታ ተቋማት ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት አድርገው ወደ ስራ በመግባታቸው እና በያዝነው ዓመት ህዝብ በስፋት የታደመባቸው ልዩ ልዩ ሁነቶች በስኬት መጠናቀቁን አስታውሷል።
የዘንድሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርቧል።