ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲክ ሾፍ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ከኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲክ ሾፍ ጋር በነበረን ውይይት በኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድ መካከል ያለውን ጠንካራ ትስስር ለማጠናከር ውይይት አድርገን ነበር።
ከኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ቁልፍ መዳረሻዎች አንዷ የሆነችው ኔዘርላንድ ኢንቨስትመንት እና የኢኮኖሚ ትብብር ለማድረግ ጉልህ አቅም አላት።
የአየር ንብረት ለውጥ ጥበቃ ሥራ ትብብርን አስመልክቶም እድሎቻችንን ለመመልከትና የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን በጉብኝቶች እና የልውውጥ መርሃ ግብሮች እንድንከውን በውይይቱ ሀሳብ አንስቻለሁ ሲሉ ገልጸዋል።