አርሰናል በኤብሪቺ ኤዜ ሀትሪክ ታግዞ ቶተንሃምን 4ለ1 አሸነፈ

You are currently viewing አርሰናል በኤብሪቺ ኤዜ ሀትሪክ ታግዞ ቶተንሃምን 4ለ1 አሸነፈ

AMN-ህዳር 14/2018 ዓ.ም

አርሰናል የሰሜን ለንደን ደርቢን በበላይነት አጠናቋል።

በ12ኛ ሳምንት የሊጉ መርሃግብር በሜዳው ኤምሬትስ ቶተንሃም ሆትስፐርስን ያስተናገደው አርሰናል 4ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

መድፈኞቹ ሙሉ ብልጫ በወሰዱበት ጨዋታ ቶተንሃምን ሊቀላቀል ተቃርቦ የነበረው ኤብሪቼ ኤዜ ሦስት ግቦችን አስቆጥሮ ሀትሪክ ሰርቷል።

የአርሰናልን ሌላኛ ግብ ሊአንድሮ ትሮሳርድ ከመረብ አሳርፏል።

በውድድር ዓመቱ ከሜዳው ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ ለተሸነፈው ቶተንሃም ብቸኛውን ግብ ሪቻርልሰን በግሩም ሁኔታ ማስቆጠር ችሏል።

በበርካቶች የውድድር ዓመቱን በዋንጫ ያጠናቅቃል የሚል ግምት የተሰጠው አርሰናል ከተከታዩ ቼልሲ በስድስት ነጥብ እርቆ ሊጉን እየመራ ይገኛል።

አርሰናል በቀጣይ በስታምፎርድ ብሪጅ ቼልሲን ይገጥማል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review