ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ የዓድዋ ድል መታሰቢያን መጎብኘታቸዉን ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ የዓድዋ ድል መታሰቢያን መጎብኘታቸዉን ገለጹ

AMN ህዳር 15/2018

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግን በክብር ተቀብለን፣ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ አስጎብኝተናቸዋል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት፣ ለጥቁር ሕዝቦች ነፃነት ትግል ዋጋ የከፈሉ ጀግኖች መታሰቢያ ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

ክቡር የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ በምድረ ቀደሞቷ ኢትዮጵያ እንዲሁም በውቧ ከተማችን አዲስ አበባ የሚኖርዎት ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review