ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት የሲንጋፖር ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግንን በክብር ተቀብያለሁ ብለዋል።
ውይይታችን በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለንን ግንኙነት ለጋራ ነጋችን ወሳኝ በሆኑ መስኮች በጋራ ለመሥራት በምናደርገው ጥረት ውስጥ አንድ ጠቃሚ ርምጃ ነው።
በተለይም በክሂሎት ልማት እና የካርበን ብድር ትብብር ላይ ያደረግናቸው የመግባቢያ ስምምነቶች ጽኑ እና ለነገው ገበያ ዝግጁ የሆኑ ሠራተኞችን ለማፍራት ብሎም በአየር ንብረት ጥበቃ ረገድ ዘላቂ፣ ዝቅተኛ ካርበን የሚያወጣ እድገት ለማረጋገጥ ያለንን የጋራ አቋም የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።
ከሲንጋፖር ጋር ይኽን የወዳጅነት እና የትብብር ጉዞ በጋራ በመቀጠላችንም ክብር ይሰማናል። በላቀ ተግባራዊ ትብብር ንግድ እና ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት፣ ዘመናዊ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስን በማልማት፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ በገንዘብ ልውውጥ ቴክኖሎጂ፣ ሳይበር ደኅንነት እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ያለንን ትብብር ለመጠቀም እጅግ ሰፊ አቅም አለን ሲሉ ገልጸዋል።