ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ኬንያ ደቡብ ሱዳንን 2ለ0 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜ ገብታለች።
የኬንያን የማሸነፊያ ግቦች ዴሪክ ዋንዮኒ እና ትሬቮር ናሳሲሮ አስቆጥረዋል።
ኬንያ ከሦስት ጨዋታ ሰባት ነጥብ በማግኘት ነው ማለፏን ያረጋገጠችው።
ውጤቱን ተከትሎ በምድቡ ተመሳሳይ ሰባት ነጥብ ያላት ኢትዮጵያም ለግማሽ ፍፃሜ አልፋለች።
ኢትዮጵያ እና ኬንያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታቸውን ረቡዕ ያከናውናሉ።
በምድብ ሁለት ቀድማ ማለፏን ያረጋገጠችው ታንዛኒያ ብሩንዲን 5ለ0 አሸንፋለች።
ታንዛኒያ አራቱንም የምድብ ጨዋታዎቿን ማሸነፍ ችላለች።
በሸዋንግዛው ግርማ