የኢትዮጵያ ባህር ኃይል እና የጣሊያን ባህር ኃይል በትምህርትና ስልጠና ዙሪያ የልምድ ልውውጥና በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የሁለትዮች የጋራ ውይይት አድርገዋል፡፡
በዚህ የሁለትዮሽ ውይይት የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ዋና አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ የጣሊያን ባህር ኃይል ከኢትዮጵያ ባህር ኃይል ጋር በጋራ ለመስራት በመምጣታቸው ታላቅ ክብር እንደተሰማቸው ገልፀዋል።
የጣሊያን የባህር ኃይል ልዑካን ቡድን መሪ በበኩላቸው አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር በተለይም በትምህርትና ስልጠና ዙሪያ ያላትን ልምድ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን በመግለፅ አገራቸው ኢትዮጵያን አጋሯ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላትም ገልፀዋል፡፡
ልዑካን ቡድኑ ጃልሜዳ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ እና ቢሾፍቱ የሚገኘውን የባህረኞች ማሰልጠኛ ማዕከል ከጎበኙ በኋላ የሁለትዮሽ ስምምነቱን ከኢትዮጵያ ባህር ኃይል ምክትልአዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሞዶር ጀማል ቱፊሳ ጋር መፈራረማቸዉን ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡