የማርበርግ ቫይረስ በሽታ (Marburg Virus Disease) ምንድነዉ?
የማርበርግ ቫይረስ ተላላፊ የሆነ የንዳድ በሽታ ነው።
ዝርያውም ፊሎቫይረስ በመባል የሚመደብ ሲሆን ከኢቦላ ቫይረስ ጋር ይቀራረባል።
ዝርያ፤ ፊሎቫይረስ (filoviruses)
የቫይረሱ ሽፋን እና ዘረመል፤ በቅባታም ኢንቨሎፕ (ሽፋን) የተጠቀለለ ሲሆን ጄኔቲክ ስሪቱ አር ኤን ኤ ነው።
ተፈጥሮዊ ምቹ፤ ቫይረሱ የሚኖረው በሌሊት ወፎች ነው። የሌሊት ወፎች ላይ በሽታ አምጭ አይደሉም።
አንዴ ወደ ሰው ከተላለፈ በሽታ ያመጣል።
ከሰው ወደ ሰውም ይተላለፋል።