ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት የሲንጋፖርን ስኬት እና ትምህርት የሚሰጡ የልማት ጉዞ ልምዶችን ከሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ ጋር “የሀገር ግንባታ፣ አለማትን ማገናኘት” በሚል ርዕስ በተሰናዳው ወግ ተካፍለናል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዎንግ በሀገር ግንባታ፣ በአመራር ዘዴ፣ በኢኮኖሚ ለውጥ እና በጂኦፖለቲካ ላይ ላካፈሏቸው ሀሳቦች ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉ ገልጸዋል።