በሞተር ሳይክል የሚፈፀሙ ወንጀሎችን መከላከል ይገባል

You are currently viewing በሞተር ሳይክል የሚፈፀሙ ወንጀሎችን መከላከል ይገባል

AMN ህዳር 16/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በከተማዋ ከሚገኙ የሞተር ሳይክል ማህበር አባላት ጋር ወንጀል መከላከልና መቆጣጠርን በተመለከተ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር፣ ለአዲስ አበባ ሰላም መጠበቅ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው፣ የሞተር ሳይክል ማህበራት ወንጀልን በመከላከል ሚናቸውን እንዲወጡ ማስቻልም አንዱ ተግባር መሆኑን አንስተዋል።

ሞተር ሳይክሎችን ለታለመላቸው አላማ ብቻ በማዋል በሞተር ሳይክል የሚፈፀሙ ወንጀሎችን መከላከል ይገባልም ብለዋል።

በመሆኑም ማህበራቱ የአዲስ አበባን ሰላም ለሌሎች ከተሞች ምሳሌ እንዲሆን ለማስቻል፣ ህገ ወጥ ድርጊት የሚፈፅሙ አካላትን ተከታትሎ ማጋለጥ እንደሚጠበቅባቸው አቶ ተስፋዬ አሳስበዋል።

በውይይቱ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የሞተር ሳይክል ማህበር አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review