የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት በመንግስት ፣ በበጎ ፈቃድ (ኢኒሼቲቭ) እና በግል ገንቢዎች (አልሚዎች) ትብብር በርካታ ቤቶችን በመገንባት በፍትሐዊነት ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው፡፡
በዚህም በተለያዩ አማራጮች ቤቶችን በመገንባት፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን በማሻሻል አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡
አስተዳደሩ ከግል ባሀብቶች ጋር በቅንጅት በመስራት፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የዜጎችን የቤት ፍላጎት ለማሟላትና ተደራሽ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
እስካሁን ድረስ በተለያዩ ፕሮግራሞች የተከናወነው ዝርዝር የሚከተለው ነው፦
በኮንዶሚኒየም ፕሮግራም:- 139,008
ለአቅመ ደካሞች እና ለአገር ባለዉለታዎች (በመንግስት እና በበጎ ፈቃደኞች ትብብር የተገነቡ):- 40,576
በከተማ አስተዳደር ለኪራይ የተገነቡ:- 24,819
በሪል እስቴት፣ በማህበር እና በግል ገንቢዎች የተገነቡ:- 175,605
በድምሩ ከ380,000 በላይ የሚሆኑ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች አስተላልፏል፡፡
በቀጣይም የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት የሚሰራ ይሆናል፡፡ – የከንቲባ ጽ/ቤት