ከኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው 3ተኛው የኢትዮጵያ የቤተሰብ ንግድ ፎረም እየተካሄደ ይገኛል።
በዘመናዊና ውስብስብ በሆነው የንግድ ዓለም ውስጥ ዘላቂ የቤተሰብ ንግድ ተቋማት እንዲገነቡ ስትራቴጂዎች፣ አሰራሮችና እና ጠንካራ አጋሮችን እንዲያገኙ ማስቻል ዓላማው ያደረገው 3ተኛው የኢትዮጵያ የቤተሰብ ንግድ ፎረም ተካሂዷል ።
በፎረሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን እስማኤል (ዶ/ር ) ኢትዮጵያ በፈጣን የለውጥ ጉዞ ላይ እንደምትገኝ ገልፀው ለዚህም የሀገር ውስጥ ባለሀብቱ ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው አያይዘውም ከውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ጎን ለጎን ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ችግር ፈቺ በሆኑ የረዥም ጊዜ ኢንቨስትመንቶች ላይ እንዲሳተፉ የመንግስት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ ጠቁመዋል።
የቤተሰብ ንግድ ዘላቂና ስኬታማ እንዲሆን አዳዲስ አሰራሮችን ከመቅረፅ ጀምሮ ከሚያጋጥማቸው ችግሮች መውጫ ሀሳቦችን ማማከር እንዲሁም አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ተቋማቸው እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የመድረኩ የክብር እንግዳ ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ የቤተሰብ ንግድ በኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሽግግር ለመፍጠር ወሳኝ አቅም መሆኑን ገልጿል፡፡
ለንግዱ ቀጣይነትም በመተማመን ላይ የተመሰረተ፣ ግልፅ አሰራርን በመዘርጋትና ስርዓት በማበጀት መምራት አስፈላጊ መሆኑን አስገዝንቧል።
ፎረሙ የኢትዮጵያ የቤተሰብ ንግድ ባለቤቶች እርስ በእርስ የሚማማሩበት፣ በጋራ ተግዳሮቶች ላይ የሚተባበሩበት እና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በጋራ አስተዋፅዖ የሚያበረክት ንቁ የቤተሰብ ንግድ ማኅበረሰብ ለመፍጠር እድል የሚሰጥ ነው።
በታምሩ ደምሴ