በአዲስ አበባ ከተማ እዉን የሆኑ ልማቶች የመንግስትን ቃል በተግባር መፈፀምን ያረጋገጡ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ልምድ የሚቀመርባቸዉ ናቸው

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ እዉን የሆኑ ልማቶች የመንግስትን ቃል በተግባር መፈፀምን ያረጋገጡ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ልምድ የሚቀመርባቸዉ ናቸው

AMN -ህዳር 17/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ እዉን የሆኑ ልማቶች የመንግስትን ቃል በተግባር መፈፀምነ ያረጋገጡ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ልምድ የሚቀመርባቸዉ መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ገለጹ፡፡

“በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ ባለፉት ቀናት ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ የፓርቲዉ ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ ልማቶችን እየጎበኙ ነዉ፡፡

አዲስ አበባ ከተማ የሰራቻቸዉ የልማት ስራዎች የመደመር እሳቤ በተግባር የተገለጠባቸዉ የሀገራዊ ብልፅግና ጉዞ ማሳያዎች ናቸዉ ብለዋል፡፡

በመዲናዋ መሰረተ ልማትን ከዜጎች ተጠቃሚነት ጋር ያሰናሰሉ ልማቶች ሀገር ካደጉት ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ የምታደርገዉን ጥረት የሚደግፉ ናቸዉ ብለዋል፡፡

በልማቶቹ ዉስጥ የአመራር ቁርጠኝነትና ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የመጨረስ ባህል በልምድ እና ተሞክሮ መልክ የሚቀመሩ ለቀጣይ ልማቶችም መነሳሳትን የሚፈጥሩ መሆኑም ተነስቷል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review