የከተማ የልማት ስራዎች የኢትዮጵያ የመልማት አቅም ማሳያዎች ናቸው

You are currently viewing የከተማ የልማት ስራዎች የኢትዮጵያ የመልማት አቅም ማሳያዎች ናቸው

AMN-ሕዳር 17/2018 ዓ.ም

የከተማ የልማት ስራዎች የኢትዮጵያ የመልማት አቅም ማሳያዎች መሆናቸው ሰልጣኝ አመራሮች ገለፁ ።

የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ የአመራር አባላት የሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች በአዲስ አበባ ከተማ የለሙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው ።

የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛና መካከለኛ አመራር አባላቱ የአራዳ ፓርክ ፣ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና ሳይንስ ሙዚየም ጎብኝተዋል።

ለኤ ኤም ኤን ሀሳባቸውን የሰጡት የብልጽግና አመራሮች የከተማ የልማት ስራዎች የኢትዮጵያ የመልማት አቅም ማሳያዎች ናቸውም ብለዋል።

በዛሬው ጉብኝታቸው የቤቶች ልማትን ፣ የጤና ተቋማትን እና የገበያ ማዕከላት የልማት ስራዎችን በመጎብኘት ላይ ናቸው።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review