የጤና ተቋማትን ተደራሽነት ለማላቅ የአዳዲስ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች ግንባታ በስፋት የተከናወነ ሲሆን የማስፋፊያ ግንባታዎችም ነባር ግንባታዎችን የሚያስንቁ ናቸው።
በዚህ ዓመት ብቻ ዘጠኝ አዳዲስ ጤና ጣቢያዎች ወደ ስራ የገቡ ሲሆን ግዙፍ የማስፋፊያ ግንባታ የተደረገላቸው ዘውዲቱን የመሳሰሉ ሆስፒታሎችም በተሟላ ሁኔታ ወደ ስራ የሚገቡበት ዕድል ተፈጥሯል።

” በቲንሽ ሆስፒታል ላይ የተገነባ ትልቅ ሆስፒታል ” በሚል የሚገለፀው የዘውዲቱ ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ የሆስፒታሉን አቅም በእጥፍ አሳድጎታል።
ዘውዲቱ ሆስፒታል ከተመሰረተበት 1934ዓ/ም ጀምሮ 261 አልጋ እና 4 የኦፕሬሽን ክፍሎች የነበሩት ሲሆን በቅርቡ የተመረቀው የማስፋፊያ ግንባታ ደግሞ 320 አልጋዎች እና 8 የኦፕሬሽን ክልሎች አሉት።

ለታካሚዎችም ለጤና ባለሙያዎችም ምቹ ሁኔታ የፈጠረው የማስፋፊያ ግንባታው ዘመኑ የደረሰበት ቴክኖሎጂዎች የተሟሉላቸው የህክምና ግብዓቶችም ተሟልተውለታል።
በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ የሁለተኛ ዙር የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ተሳታፊዎች እነዚህን እና ሌሎች የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡