የማይተዋወቁ ሰዎች በጋራ ማዕድ የሚጋሩበት ምግብ ቤት

You are currently viewing የማይተዋወቁ ሰዎች በጋራ ማዕድ የሚጋሩበት ምግብ ቤት

AMN- 17/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከማያውቁት ሰው ጋር በአንድ መዓድ የሚመገቡበት ምግብ ቤት ስለመኖሩ ያውቃሉ?

አብሮ መብላት አብሮ መጠጣት እና ተካፍሎና ተደጋግፎ መኖር የኢትዮጵያውያን አንዱ መገለጫ ባህል ነው።

አብሮ የመብላት ባህልን ከሚያጎሉ ተግባራት መካካል አንዱ ወደ ሆነው የአዲሰ አበባ ሌላኛው መልክ ሆነው ምግብ ቤት ጎራ ካሉ እገሌን አውቀዋለሁ ወይንም አላውቀውም ሳይሉ ሰላምታ ተለዋውጦ በጋራ መዓድ የሚቋደሱበት ቤት ነው።

የዚህ አብሮ የመመገብ ባህል ማሳያ የሆነው ወ/ሮ ዙርያሽ አበጋዝ የእሙዬ ማጀት ምግብ ቤት ባለቤት ናቸው ስራውን ከጀመሩት ስድስት ዓመት እንደሆናቸው ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል ።

እስከ ሀያ ሰው በአንድ ጊዜ መመገብ በሚችል ትሪ ምግብ በማቅረብ ሰዎች በጋራ እንዲመገቡ እንደሚያደርጉ የነገሩን ወ/ሮ ዙርያሽ፣ ይህ አብሮ የመብላት ባሕል አብሮነትን እንደሚያጠናክር እና በእርሳቸው ቤት አብረው የሚበሉ ሰዎች ማህበራዊ ትስስርን እንደሚፈጥሩ አብራርተዋል።

ይህንን ለማድረግ ያነሳሳቸውም ከአስተዳደጋቸው ጀምሮ ከቤተሰባቸው ጋር አብሮ በአንድ ገበታ የመመገብ ልምድ መሆኑንና ይህንንም ለማስቀጠል በማሰብ ስራውን እንደጀመሩት ነው ያጫወቱን ።

ለተመጋቢዎች የሚያቀርቡትን እንጀራ እንደማይቆጥሩ የተናገሩት ወ/ሮ ዙርያሽ፣ ባሕላችንን እናክብር አብሮነት፣ መከባበር እና መዋደድ የማንነታችን መገለጫ በመሆኑ ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ ያደረጉት የምግብ ቤቱ ተጠቃሚዎች በጋራ መአድ መቋደሱ አዳዲስ ሰዎችን እንዲተዋወቁና ማህበራዊ ትስስራቸውም እንዲሰፋ እንዲሁም የፍቅር ግንኙነት እስከ መመስረት መድረሳቸውንም ነው የተናገሩት።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review