በኢትዮጵያ የተከሰተዉን የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከል እስካሁን ድረስ ምን ተከናወነ ?

You are currently viewing በኢትዮጵያ የተከሰተዉን የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከል እስካሁን ድረስ ምን ተከናወነ ?
  • Post category:ጤና

AMN ህዳር 17/2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ በደቡብ ክልል የተከሰተዉን የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከል እስካሁን ድረስ ምን ተከናወነ??

👉 የመጀመሪያው የበሽታው ታማሚ ከተገኘበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በበሽታው ለተጠረጠሩ ለ73 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል

👉 11 በሚሆኑ ግለሰቦች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘ ተረጋግጧል

👉 እነዚህ ታማሚዎች አስፈላጊው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ቢሆንም የ6ቱ ህይወት አልፏል

👉 የተቀሩት 5ቱ ደግሞ በህክምና ጣቢያ ወስጥ ሕክምናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ

👉 የበሽታው ምልክቶች ከታየባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው 349 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል

👉 ከእነዚህም ውስጥ 119ኙ የክትትል ጊዜያቸውን ጨርሰው ከለይቶ ማቆያ እንዲወጡ ተደርጓል

👉 ወረርሽኙን በአጭር ጊዜ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የተለያዩ ተቋማትን እና የሙያ ስብጥርን ያካተተ ከፍተኛ ፈጣን ምላሽ ሰጭ ቡድን ተደራጅቷል

👉 የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል

👉 ማህበረሰብአቀፍ የቅኝት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ

👉 ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እየተከናወነ ይገኛል

👉 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የማከም ስራ እየተሰራ ነዉ

👉 ከቫይረሱ ጋር ንክኪ ያላቸዉን ሰዎች የመለየት ስራዎች እየተሰሩ ነዉ

👉 በብሔራዊ እንዲሁም በክልል ደረጃ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች የክስተት አስተዳደር ስርዓት (Incident Management System)ተቋቁሞ የፈጣን ምላሽ ስራዎችን በማስተባበር ላይ ይገኛል።

👉 የላቦራቶሪ የመመርመር አቅምን ከማሳደግ አኳያ የቫይረሱን ዘረ መል ለመለየት የሚያስችል የላቦራቶሪ አቅም ተገንብቷል

👉 ተንቀሳቃሽ የላቦራቶሪ መመርመሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ግብአቶችን ወደክልሉ ተልከዋል

👉 የተሰበሰቡት ሁሉም ናሙናዎች ረጅም ርቀት ሳይጓጓዙ ባሉበት ቦታ ለመመርመር ተችሏል

👉 የበሽታውን መነሻ ለማወቅም አሁንም ጥረቶች እና ምርመራዎች እየተደረጉ ነዉ

👉 ወረርሽኙ በተሰተባቸው አካባቢዎች የለይቶ ማከሚያ ማዕከላትን በማቋቋምና የሰለጠነ የሰውሃይል እና አስፈላጊውን የህከምና ግብአት በማደራጀት ለታማሚዎች የተጠናከረ የህክምና እርዳታ እየተሰጠ ይገኛል

👉 ለታማሚዎችም የተሻለ ሕክምና ለመስጠት ከዚህ በፊት ወረርሽኙ ተከስቶባቸው ከነበሩ ሀገራት ጋር የልምድ ልውውጥ ተደርጓል

👉 የተገኘዉን ልምድ በመቅሰም ከዚህ በፊት ተሞክረው ጥሩ ውጤት ያስገኙ መድኃኒቶችንና ክትባቶችን በመለየትና ወደሃገር ውስጥ በማስገባት ለታካሚዎች ተደራሽ እየሆኑ ይገኛሉ

👉 በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ከነበራቸው የማህበረሰብ አካላት ጋር በበሽታው የመያዝ እድላቸውን ለመቀነስ የሚያግዝ Remsedevir የተባለ የፀረ ህዋስ መድሃኒት ወደ ሃገራችን ውስጥ ገብቷል

👉 እስካሁን 16 ለሚሆኑ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ተብለው ለታሰቡ የህክምና ባለሙያዎች እና ታማሚዎች ለማድረስ ተችሏል

👉 በሽታው ባልተገኘባቸው የሀገሪቱ ክፍሎች ወደፊት በሽታው ቢከሰት ሀከምና ለመስጠት የሚያስችሉ የለይቶ ማከሚያ እና ማቆያ ማዕከላት በሰለጠነ የሰው ሃይል፥ በግብዓትና በሌሎች ቁሳቁሶች እንዲሟሉ እየተደረገ ይገኛል

👉 የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ከሕብረተሰቡ ጋር ከሚደረገዉ የቅኝትና ልየታ ስራ በተጨማሪ በአገር በመውጫና መግቢያ ኬላዎች፥ በአየር ማረፊያዎች፥ እና ወረርሽኙ በተገኘባቸው አካባቢዎች የሚወጡና የሚገቡ ሰዎችን፣ ኬላዎችን በማቋቋም ሰፊ የልየታ ስራዎችን እየተሰሩ ይገኛሉ

👉 በሚቀጥሉት ሳምንታት ከሚካሄደው ሀገር አቀፍ የፖሊዮ ዘመቻ ጋርም በማስተሳሰር የቅኝትና የልየታ ተግባራት በሰፊው የሚከናወኑ ይሆናል።

ምንጭ – የጤና ሚኒስቴር

#Ethiopia

#addisababa

#health

#MarburgVirus

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review