የብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ስናከብር ሁሉንም ባካተተና በእኩልነት ሊሆን ይገባል አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር ገለጹ፡፡
አፈ ጉባኤዋ 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ በለሚ የበጎነት መንደር ለሚኖሩ አቅመ ደካማ ዜጎች ማዕድ አጋርተዋል።
ከተማዋ የተለያዩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መኖሪያ እንደመሆኗ ሁሉንም በእኩልነት ለማሳተፍ እየሰራች ነው ብለዋል።

የምገባ ማዕከላትን ጨምሮ በመዲናዋ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ሁሉም በእኩልነት ሊገለገልባቸው የሚችሉ ስለመሆኑም አፈጉባኤዋ አንስተዋል።
አብሮ መብላት መጠጣት ፣መረዳዳት ኢትዮጵያዊ ባህል እና መገለጫ ሆኖ ዘመናትን ዘልቋል። አዲስ አበባም በጎነትን ልምድና ባህል ካደረገች ዋል አደር ብላለች።
በጽዮን ማሞ