ኢትዮጵያ ኬንያን በማሸነፍ ምድቧን በበላይነት አጠናቀቀች

You are currently viewing ኢትዮጵያ ኬንያን በማሸነፍ ምድቧን በበላይነት አጠናቀቀች

AMN-ህዳር 17/2018 ዓ.ም

ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዋን ከኬንያ ጋር ያደረገችው ኢትዮጵያ 1ለ0 አሸንፋለች።

በውድድሩ ድንቅ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘው ዳዊት ካሳው የጨዋታውን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።

አጥቂው በውድድሩ ያስቆጠራቸውን ግቦች ብዛት ሰባት አድርሷል።

ኢትዮጵያ ምድብ አንድን በ10 ነጥብ የበላይ ሆና ስታጠናቅቅ ፣ ኬንያ በሰባት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ይዛ ለግማሽ ፍፃሜው አልፋለች።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review