አቶ ኩመራ ዋቅጅራ የልዑል ዊልያም የአፍሪካ ጥበቃ ሽልማት አገኙ

You are currently viewing አቶ ኩመራ ዋቅጅራ የልዑል ዊልያም የአፍሪካ ጥበቃ ሽልማት አገኙ

AMN – ሕዳር 18/2018 ዓ.ም

አቶ ኩመራ ዋቅጅራ በኢትዮጵያና በትልቁ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ለዱር እንስሳት ጥበቃ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የ2025 የልዑል ዊልያም የአፍሪካ ጥበቃ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።

በምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ የተወለዱት አቶ ኩመራ፣ በአገሪቱ ብሔራዊ የዱር እንስሳት ፖሊሲን በማዘመን፣ የሕዝብን አመለካከት በመለወጥ፣ የሬንጀር (ዘብ) አቅምን በማጠናከር እና ለአደጋ የተጋለጡ ዝርያዎችንና መኖሪያዎችን ለመጠበቅ አዳዲስ መፍትሄዎችን በማፍለቅ ላከናወኑት ሃገራዊ ተግባር እጅግ የተገባ ሽልማት ማግኘታቸው ተገልጿል፡፡

አቶ ኩመራ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን (EWCA) ዋና ዳይሬክተር ናቸው።

በ27 ብሔራዊ ፓርኮች ውስጥ የዱር እንስሳት ቆጠራ ለማካሄድ፣ ፕሮጀክቶችን ለመከታተል እና በአካባቢው ከሚኖሩ ማኅበረሰቦች ጋር ለመገናኘት በአካባቢዎቹ በተደጋጋሚ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ለተፈጥሮ ጥበቃ ልማት ትኩረት በሰጠች አገር ውስጥ እንደ ዘላቂ ዕድገትና ባህላዊ ማንነት አድርገው መሥራት ችለዋል፡፡

በባለድርሻ አካላት ዘንድ የጥበቃን አስፈላጊነት ግንዛቤ በማሳደግ ሰፊ ድጋፍ አግኝተዋል።

የተፈጥሮ ጥበቃ የትብብር ጥረት ነው የሚሉት አቶ ኩመራ ስኬቱ የሚወሰነው በቁርጠኝነት መንፈስ እና ዝርያዎችን ብቻ ሳይሆን የሰዎችን ደህንነት በመጠበቅ የኃላፊነት ስሜት ሲኖር ጭምር መሆኑን ያምናሉ፡፡

በራዕያቸውም ታማኝነትና የማይታክት ቁርጠኝነት፣ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ተጠናክሯል እንዲሁም በአፍሪካ ውስጥ ትብብር እንዲፈጠር አነሳስቷል።

በተፈጥሮ ጥበቃ ረገድ ባበረከቱት ላቅ ያለ አስተዋፅዖም የ2025 የልዑል ዊልያም የአፍሪካ ጥበቃ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review