3ኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት በአዲስ አበባ መካሄዱ የኢትዮጵያን የልማት ስኬቶችና ቀጣናውን ለማስተሳሰር እያከናወነቻቸው ያሉ ውጤታማ ተግባራትን አጉልቶ ለማሳየት መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ኢጋድ ኢትዮጵያ የዘንድሮውን የሚዲያ አዋርድ እንድታስተናግድ መምረጡ በአረንጓዴ ዐሻራ እና ሌሎች የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ስራዎች ላከናወነቻቸው ስኬታማ ተግባራት እውቅና የሰጠ መሆኑንም ገልጿል።
የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡