ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን አከባበር ህብረ ብሄራዊነትን የሚያጠናክር እና የጋራ ትርክትን የሚያሰርፅ እየሆነ መምጣቱን ያነጋገርናቸው የየካ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
የየካ ክፍለ ከተማ ምክር ቤትም “ዴሞክራሳዊ መግባባት፤ ለህብረ ብሄራዊ አድነት” በሚል መሪ ሀሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን 20ኛውን የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት እያከበረ ይገኛል፡፡
ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን አከባበር ህብረ ብሄራዊነትን የሚያጠናክር እና የጋራ ትርክትን የሚያሰርፅ እየሆነ መምጣቱን የተናገሩት የተለያዩ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች አባላት ናቸው፡፡
ባለፋት ጥቂት አመታት እለቱን ከማክበርም ባሻገር፣ የሁሉንም ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች መሰራታቸውንም ገልፀዋል፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ እለቱን በተለያዩ መርሀ ግብሮች በማክበር ተጀምሯል፡፡
በራሄል አበበ