የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን እንደ ከተማም፣ እንደ ሃገርም በርካታ ስኬቶች በተመዘገቡበት ማግስት የሚከበር መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ተገልጿል።
20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጉለሌ ክፍለ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሪት ፈይዛ መሃመድ፣ የዘንድሮው በዓል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ የአዲስ አበባ ከተማን ብሎም የኢትዮጵያን ገፅታ የቀየረው የኮሪደር ልማት እና ሌሎችም ስራዎች ፍሬያቸው በታየበት ማግስት የሚከበር መሆኑን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ከተባበሩ ታላቅ የሆነ ሀገራዊ ስኬት ማስመዝገብ እንደሚችሉ የገለጹት ምክትል አፈ ጉባኤዋ፣ ትውልዱ ለሃገር አንድነት፣ ሰላምና ለእድገት ሊሰራ እንደሚገባም በአፅንዖት ተናግረዋል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ባዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ የተለያዩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ባህላዊ ምግቦች፣ አልባሳት፣ ጭፈራዎች፣ እና ሌሎችም ትርዒቶች ቀርበዋል፡፡
በመቅደስ ደምስ