የህብረት ስራ ማህበራትን አሰራር በማዘመን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸውን ማሳደግ ይገባል፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ የዘርፉ ባለሙያዎችን አቅም የሚያጐለብት ሥልጠና በአዳማ ከተማ እየተሰጠ ይገኛሉ፡፡
ስልጠናው ባለሙያዎቹ የአምራቾችን ችግር በመፍታት እና አቅም በማጎልበት በሀገር አቀፍ ደረጃ የምርት አቅርቦትን በማሳደገ የኑሮ ውድነትን ለመከላከል እንደሚሰሩ የሚያስችል ነው፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ ማዕከላት መሰጠት የጀመረው ስልጠናው ከ3 ሺህ 200 በላይ ባለሙያዎችን በመጀመሪያው ዙር ተደራሽ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ከአራቱ የስልጠና ማዕከላት አንዱ በሆነው በዛሬው ዕለት በአዳማ መሰጠት በጀመረው ስልጠና ከ960 በላይ የህብረት ስራ የልማት አመቻች ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ስልጠናው በሁለት ዙር 10ሺህ የሚጠጉ የልማት አመቻች ባለሙያዎች ተደራሽ እንደሚያደርግ ተነግሯል።
በአዳማ ከተማ እየተሰጠ ባለው ስልጠና እየተሳተፉ ያሉት ሰልጣኞች ከኦሮሚያ ክልል እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተውጣጡ ባለሙያዎቸ መሆናቸው ተገልጿል።
ይህ እየተሰጠ ያለው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ የልማት አመቻች ባለሙያዎች ስልጠና ለ12 ቀናት የሚዘልቅ መሆኑም ተገልጿል።
በአሰግድ ኪዳነማሪያም