ስኬት ባንክ አጠቃላይ የካፒታል መጠኑ 9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታወቀ

You are currently viewing ስኬት ባንክ አጠቃላይ የካፒታል መጠኑ 9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታወቀ

AMN ሕዳር 22/2018 ዓ.ም

ስኬት ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አጠቃላይ የካፒታል መጠኑ 9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታወቀ።

ባንኩ 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዷል።

የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጥላሁን ወርቁ ስኬት ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አጠቃላይ የካፒታል መጠኑ 9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መድረሱን ተናግረዋል።

የባንኩ የተከፈለ የካፒታል መጠን ከ6 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ወደ 7 ነጥብ 84 ቢሊዮን ብር ማደጉን እንዲሁም ጠቅላላ የደንበኞች ቁጥር 615 ሺህ ማድረስ መቻሉን ለጉባዔው ላይ ባቀረቡት አመታዊ የስራ ሪፖርት አንስተዋል።

ስኬት ባንክ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 1 ነጥብ 24 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡንም ባንኩ ለኤኤምኤን በላከው መረጃ አስታዉቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review