በሆንግ ኮንግ በደረሰ የእሳት አደጋ የሟቾች ቁጥር 151 መድረሱን ተከትሎ ተጨማሪ ተጠርጣሪዎች ለእስር ተዳርገዋል

You are currently viewing በሆንግ ኮንግ በደረሰ የእሳት አደጋ የሟቾች ቁጥር 151 መድረሱን ተከትሎ ተጨማሪ ተጠርጣሪዎች ለእስር ተዳርገዋል

AMN- ህዳር 22/2018 ዓ.ም

በሆንግ ኮንግ በመኖሪያ ህንፃዎች ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የሟቾች ቁጥር 151 መድረሱን ተከትሎ ተጨማሪ ተጠርጣሪዎች እየታሰሩ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የሆንግ ኮንግ ባለስልጣናት በከተማዋ በአስርት ዓመታት ውስጥ ተከስቶ በማያውቀው እና ባለፈው ሳምንት በተከሰተው ከባድ የእሳት አደጋ፣ 13 ሰዎች በግድያ ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸውን ገልጸዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ህንፃዎችን ለማደስ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ቁሳቁሶች ጥቅም ላይ በማዋል በትንሹ የ151 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የእሳት ቃጠሎ እንዲባባስ ምክንያት መሆናቸውን ነው ባለስልጣናቱ የጠቆሙት ፡፡

በህንፃ እድሳት ላይ የተሰማሩ ኮንትራክተሮች ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ደረጃቸውን ያልጠበቁ ቁሳቁሶችን ከተቆጣጣሪዎች በመደበቅ ይጠቀሙ ነበር ሲሉ አንድ ባለስልጣን ተናግረዋል ፡፡

ፖሊስ በእሳት አደጋው በወደሙ ሰባት ህንፃዎች፣ እሳቱን ለመሸሽ ሲሞክሩ በህንፃ መወጣጫ ደረጃዎች እና ጣራ ላይ ተቃጥለው ህይወታቸው ያለፈ ነዋሪዎችን አስከሬኖች ማግኘቱን ቀጥሏል፡፡

እስከ አሁንም ከ40 በላይ ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁ ነው የተገለፀው ፡፡

የፖሊስ አዛዡ ሳንግ ሹክ ዪን፣ አንዳንድ አስከሬኖች ወደ አመድነት እንደተቀየሩና የጠፉ ሰዎችን ለመለየት እንደተቸገሩ ለጋዜጠኞች መግለፃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review