የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ከሰራተኞች ስነምግባር እና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚነሱ የግብር ከፋይ ቅሬታዎችን መፍታት የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መዘርጋቱን አስታወቀ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ከሰራተኞች ስነምግባር እና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚነሱ የግብር ከፋይ ቅሬታዎችን መፍታት የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መዘርጋቱን አስታወቀ

AMN ህዳር 22/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ከሰራተኞች ስነምግባር እና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚነሱ የግብር ከፋይ ቅሬታዎችን መፍታት የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መዘርጋቱን አስታዉቋል፡፡

ጽ/ቤቱ ከአዲስ አበባ የግብር አሰባሰብና የገቢዎች አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ማንኛዉም አይነት ቅሬታ መፍታት የሚያስችል አዲስ አሰራር በከንቲባ ፅ/ቤት ስር መዋቀሩን አስታዉቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ ስር የተዘረጋዉ የቅሬታ አፈታት ስርዓት እንደተጠበቀ ሆኖ በዛ ያልረካ ግብር ከፋይ ከንቲባ ፅ/ቤት ማንኛዉንም አይነት ከገቢ አሰባሰብ ፣ ከሰራተኞች ስነምግባር እና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚነሱ የግብር ከፋዮች ቅሬታዎችን ለመፍታት ዘወትር ሐሙስ ኃላፊዎች በተገኙበት የሚደመጥ እና ተጣርቶ ምላሽ የሚሰጥበትን አሰራር መዘርጋቱን ነው ጽ/ቤቱ ያስታወቀዉ፡፡

ሁልጊዜም የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የሚተጋዉ እና ህዝብን አዳምጦ ምላሽ መስጠትን የትኩረት ማእከሉ ያደረገዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከንቲባ ፅ/ቤት በሚስጥር ጥቆማ የሚሰጥበትን ነፃ የጥሪ ማእከል 9977 ፣ የሚስጥር ሳጥንን ጨምሮ በተጨባጭ ቅሬታዉን በአካል ለበላይ አመራር ማቅረብ የሚችልበትን አሰራር የፊታችን ሐሙስ ጀምሮ ወደ ተግባር እንደሚገባ ገልጿል፡፡

በመሆኑም ከመጪዉ ሐሙስ ህዳር 25/2018 ጀምሮ ጠዋት ከ 2 ሰአት እስከ 7 ሰአት ድረስ ከገቢዎች ጋር ብቻ የተያያዘን ቅሬታ አመራሩ ተቀብሎ የሚስተናግድ መሆኑን በመረዳት በከንቲባ ፅ/ቤት ተጨባጭ ቅሬታ ያላቸዉ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን የከተማዉ አስተዳደሩ አሳዉቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለቀልጣፋ እና ፍትኃዊ አገልግሎት እንደሚተጋ ጨምሮ ገልጿል፡፡

#addisababa

#Ethiopia

#revenue

#incometax

#service

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review