የ2018 ዓ.ም የሐጅ ጉዞ ምዝገባ ተጀመረ

You are currently viewing የ2018 ዓ.ም የሐጅ ጉዞ ምዝገባ ተጀመረ

AMN – ህዳር 22/2018 ዓ.ም

የ2018 ዓ.ም የሐጅ ጉዞ ምዝገባ ከዛሬ ህዳር 22/ 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ጣቢያዎች የተጀመረ መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2018 ዓ.ም የሐጅ ጉዞ ምዝገባ መጀመሩን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ አብዱልከሪም በድረዲን፤ምዝገባው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

ለሐጅ ጉዞ መስፈርቱን የሚያሟሉ ሁሉ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው ቀነ ገደብ መመዝገብ እንዳለባቸው ተናግረዋል።መረጃው የኢዜአ ነው ፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review