በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ተይዘው የነበሩ ሁለት ወጣቶች አገግመው ከህክምና ማዕከል ወጡ

You are currently viewing በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ተይዘው የነበሩ ሁለት ወጣቶች አገግመው ከህክምና ማዕከል ወጡ
  • Post category:ጤና

AMN ህዳር 22/2018

‎በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ተይዘው የነበሩ ሁለት ወጣቶች አገግመው ከህክምና ማዕከል መዉጣታቸዉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የ 19 አመት ወጣት ኢዩኤል ኤቃል እና የ16 ዓመት እህቱ የሱሥራ ኤቃል በማርበርግ በሽታ ተይዘው በለይቶ ማቆያ የህክምና ድጋፍ ሲደረግላቸው የነበረ ሲሆን ሁለቱም ወጣቶች ከማርበርግ ቫይረስ በሽታ ነፃ መሆናቸው መረጋገጡን ሚኒስቴሩ ለኤኤምኤን ዲጂታል ሚዲያ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ እንደገለፁት ሁለቱ ወጣቶች ቀደም ሲል በማርበርግ በሽታ ቫይረስ ተይዘው ህይወታቸው ካለፈ አባታቸው ጋር ንክኪ የነበራቸው ሲሆኑ የበሽታውን ምልክት አሳይተው የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ቫይረሱ ስለተገኘባቸው የህክምና ክትትል ሲያደርጉ እንደነበር አስረድተዋል።

ከእነዚህ ወጣቶች በተገኘ ልምድ ማንኛውም የበሽታ ምልክት የሚታይባቸው ግለሰቦች ፈጥነው ወደ ጤና ተቋም ቢሄዱ የመዳን ዕድላቸውን እንደሚያሳድግ የገለፁት አቶ እንዳሻው ህብረተሰቡ ከመዘናጋት ወጥተው የቫይረሱ ምልክት እንደ ታየ ወደ ጤና ተቋም ሊመጡ ይገባል ብለዋል፡፡

የቢሮ ሀላፊው የጤና ባለሙያዎችን፣ በተግባሩ የተሳተፉትን አመራሮችን ጨምሮ ጤና ሚኒስቴር፣ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትንና አጋር ድርጅቶችን አመስግነዋል፡፡

#Ethiopia

#addisababa

#health

#marburg

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review