ታዳጊዎቹ ከ22 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ኬንያን ይገጥማሉ

You are currently viewing ታዳጊዎቹ ከ22 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ኬንያን ይገጥማሉ

AMN ኅዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተከናወነ የሚገኘው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ዛሬ ይጠናቀቃል።

በዩጋንዳ ተሸንፋ ለፍፃሜ ማለፍ ያልቻለችው ኢትዮጵያ 3ኛ ደረጃ ይዞ ለማጠናቀቅ ኬንያን ትገጥማለች።

ኢትዮጵያ ጨዋታውን በድል ከተወጣች ከ22 ዓመታት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ትሳተፋለች።

ኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችው እኤአ 2003 ስዋዚላንድ /እስዋቲኒ/ ባዘጋጀችው መድረክ ላይ ነበር።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚከናወነው የዛሬ ጨዋታ ቀን 6 ሰዓት ላይ ይጀምራል።

ብሩህ ጊዜ የሚጠብቃቸው ታዳጊዎቹ ድጋፍ እንደሚፈልጉ አሰልጣኙ ቤንጃሚን ዚመር ጥሪ አቅርበዋል።

የፍፃሜው ጨዋታ ቀን 9:30 ላይ ይጀምራል። ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ ዋንጫ ለማንሳት ይፋለማሉ።

ጨዋታውን ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ ይመሩታል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review