በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት መርሃግብር ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።
ማንችስተር ሲቲ ወደ ምዕራብ ለንደን አቅንቶ ፉልሃምን ይገጥማል።
ባሳለፍነው ቅዳሜ ሊድስ ዩናይትድን ተቸግሮ 3ለ2 ያሸነፈው ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ድል ካደረገ ከአርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ያጠባል።
ሲቲ ከፉልሃም ጋር ያደረጋቸውን የመጨረሻ 10 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሁሉንም አሸንፏል።
በክራቫን ኮቴጅ የሚደረገው የዛሬ ጨዋታ ምሽት 4:30 ላይ ይጀምራል።
በተመሳሳይ ሰዓት ካለፉት አራት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ያገኘው ቦርንማውዝ በሜዳው ቪታሊቲ ስታዲየም ኤቨርተንን ያስተናግዳል።
ምሽት 5:15 ላይ ኒውካስትል ዩናይትድ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ይጫወታሉ።
ሁለቱም ክለቦች እኩል 18 ነጥብ በመሰብሰብ በደረጃ ሰንጠረዡ 12 እና 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
በሸዋንግዛው ግርማ