የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ኮሚሽነር ጀነራል የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነትን የበለጠ በማጠናከር ሽብርተኝነትንና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል፣ በልምድ ልውውጥ፣ በአቅም ግንባታ በትብብር አብሮ ለመስራት ከአምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በበኩላቸው የሁለቱን ሀገራት ፖሊስ ለፖሊስ ግንኙትን የበለጠ ለማሳደግ ሀገራቸው ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገልፀው በተለይም ሽብርተኝነትና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ እና በትብብር ለመከላከል አሜሪካ ቁርጠኛ መሆኗን በውውይቱ ወቅት ማረጋገጣቸዉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል፡፡