ከ100 ሀገራት በላይ የሚሳተፉበት የአለም ወንዶች ቦክስ ሻምፒዮና ነገ ይጀምራል።

You are currently viewing ከ100 ሀገራት በላይ የሚሳተፉበት የአለም ወንዶች ቦክስ ሻምፒዮና ነገ ይጀምራል።

AMN_ህዳር 24/2018 ዓ.ም

በዱባይ ሀገር ለሚካሄደው የ2025ቱ የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያ በ5 ተወዳዳሪዎች እና ሁለት አሰልጣኞች ትወከላለች።

ጠንካራ ፋክክር በሚጠበቅበት አመታዊ ሻምፒዮና ቦክሰኛ አቤል አባትዬ በ48 ኪ.ግ፣

ያብስራ ታደለ በ51 ፣ዘከርያ ከድር በ54፣ ሀይማኖት ደሳለን በ57፣ ስራዊት ፀጋ በ60 ኪ.ግ የሚፈለሙ ቦክሰኞች ሲሆን ዋና ኢንስፔክተር ቴዎድሮስ ጥላሁን እና

ዋና ኢንስፔክተር መኮንን ጌታቸው የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኞች ናቸው።

የኢትዮጵያ ቦክስ ፌደሬሽን የፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ተስፋዬ የቡድን መሪ በመሆን በስፍራው ይገኛሉ።

ደማቅ የመክፈቻ የነበረው ፕሮግራሙ ላይ ከ108 ሀገራት የተገኙ 428 ብጢኞች ከባድ ፍልሚ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በፕሮግራሙ መደበኛ ጉባኤ ስለሚካሄድ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌደሬሽን ከፍተኛ አመራሮች ይታደሙበታል።በእለቱም ታላላቅ ፕሮፌሽናል ቦክሰኞች ውድድር እንዲያደርጉ መርሃግብር ወቶላቸዋል።

ኢትዮጵያ ነገ በመክፈቻው ዘከርያ ከድር በ54 ኪ.ግ ከኬኒያ አቻው ጋር በሚያደርገው ውድድር በይፋ ትጀምራለች።

በዮናስ ሞላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review