በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።
በፓናል ውይይቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሪት ፋይዛ መሀመድ፣ “ያልተገባ ሀብት ለማካበት መጣር ለሀገር ዕድገት ከፍተኛ እንቅፋት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ትግል ሊያደርግ ይገባል” ብለዋል።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ኃላፊዎችና አባላት፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉበት ነው።
ምክትል አፈ ጉባኤዋ እንደገለጹት፣ በአዲስ አበባ ባለፉት ዓመታት በተደረገው የፀረ-ሙስና ትግል ሊመዘበር የነበረ የህዝብና የመንግስት ሀብቶችን በማዳን በከተማዋ በአጭር ጊዜ ፈጣን ዕድገት ማስመዝገብ ተችሏል።

ሙስናን ለመከላከል በተሰራው ስራ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ እና 57 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ከምዝበራ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል።
በመጨረሻም “ያልተገባ ሀብት ለማካበት መጣር ለሀገር ዕድገት ከፍተኛ እንቅፋት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ትግል ሊያደርግ ይገባል” በማለት ጥሪ አቅርበዋል።
በየአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የትግሉን ሂደት አስመልክቶ አስታውቋል።
ሙስናን ለመከላከል በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች ተሰርተዋል።
በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ሰራተኞች ሀብታቸው እንዲያስመዘግቡ ተደርጓል።
በብልሹ አሰራር ውስጥ ገብተው የተገኙ ከ12 ሺህ በላይ ከፍተኛ አመራሮች እና ደላሎች ከቀላል ዲሲፒሊን እስከ ከፍተኛ የወንጀል ክስ ተጠያቂ መደረጋቸውንም ኮሚሽኑ አሳውቋል።
በአሰግድ ኪ/ ማርያም