ኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ኤክዝኪውቲቭ ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች

You are currently viewing ኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ኤክዝኪውቲቭ ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች

AMN – ሕዳር 25/2018 ዓ.ም.

የዓለም ምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) ባካሄደው 179ኛ የካውንስል ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ኤክዝኪውቲቭ ቦርድ አባል ሆና በሙሉ ድምጽ መመረጧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ቦርድ አባል ሆና በመመረጧ በዓለም አቀፉ የረሀብና የምግብ ዋስትና ቀውስ አያያዝ ዙሪያ ውሳኔ በሚሰጥበት ጉባዔ ላይ በቀጥታ የመሳተፍ ዕድል ታገኛለች። ምርጫው የተካሄደው በሮም በሚገኘው የዓለም ምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) ዋና መስሪያ ቤት ሲሆን በስብሰባው ላይ የተገኙት ሁሉም አባል አገራት በኢትዮጵያ ምርጫ ላይ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ የዓለም ምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) ከተመሠረተ 3 ዓመት በኋላ በ1940 ዓ.ም. ከሰሀራ በታች ቀዳሚዋ የአፍሪካ ሀገር ሆና መቀላቀሏ ይታወቃል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review