የአፍሪካ ሕብረት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት /አፋህድ/ መካከል ለተፈረመው የሰላም ስምምነት ያለውን አድናቆት ገለጸ

You are currently viewing የአፍሪካ ሕብረት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት /አፋህድ/ መካከል ለተፈረመው የሰላም ስምምነት ያለውን አድናቆት ገለጸ

AMN – ሕዳር 25/2018 ዓ.ም.

የአፍሪካ ሕብረት በዛሬው ዕለት በክልሉ መንግስት እና በድርጅት መካከል ለዘላቂ ሰላም የሚበጅ ስምምነት መፈረማቸው ኢትዮጵያ የሰላም ጉዞ ለማድረግ አንድ ትልቅ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሷን የሚደግፈው ሀሳብ መሆኑን በገጹ ላይ አስፍሯል።

የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ሲካሄድ አሕጉራዊውን ድርጅት በመወከል የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር ክብርት ሰልማ ማሊካ ሀዳዲ እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ምክትል ዋና ፀሐፊ አቶ መሐመድ አብዲ ዋሬ ተገኝተው ነበር።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ሊቀ-መንበሯ ለውይይትና ሰላማዊ መፍትሔ ሁለቱ ወገኖች ላሳዩት ፅናትና ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን በመግለጽ “ይህ ስምምነት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው የአፍሪካ አሕጉር ወሳኝ ምዕራፍ ነው” ብለዋል።

“እያንዳንዱ የሰላም ስምምነት ‘አፍሪካ የጦር መሳሪያ ድምጽ የማይሰማባት አሕጉር’ ለማድረግ የጀመርነውን ግባችንን ያሳካልናል” ብለዋል።

ክብርት ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ በአፍሪካ ሕብረት ስም ሁለቱንም ወገኖቹን እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት ስኬቱ ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ የመስጠት ኃይል እንዳለን ያሳያል ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review