በአፍሪካ ሚዲያ አዋርድ በልዩ ካታጎሪ ሽልማት (Special Category Awards) የኢቢሲዋ ጋዜጠኛ መታሰቢያ ደረጀ አሸናፊ ሆናለች።
በምርጥ የቪድዮ ፕሮዳክሽን ዘርፍ ከሩዋንዳ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሂርዋ አይማብሌ አሸናፊ ሆኗል።
በአፍሪካን ኢንዲፔንደንት ዘርፍ (African Independent Category) ልዩ ዘርፍ ደግሞ ኩዳክዋሼ ሞዮ ከዚምባቡዌ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አሸንፏል።
ከ40 ሀገራት የተወጣጡና በተለያዩ ዘርፎች በውድድሩ ተሳታፊ ከነበሩ ከ800 በላይ የሚዲያ ባለሙያዎች መካከል 21ንዱ እጩዎች በተለያዩ ምድቦች ዛሬ ለፍጻሜ ደርሰዋል።
የአፍሪካን ሰላም፣ ልማት እና ተጠቃሚነት መሰረት ያደረጉ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ስራዎች የሽልማቱ አካል ሲሆኑ፣ በፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ የሚታወቁ ግለሰቦችና ተቋማትም በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።
የአፍሪካ ህብረት ብሮድካስቲንግ፣ የፓትሪስ ሉሙምባ ፋውንዴሽን፣ የክዋሜ ንክሩማህ ፋውንዴሽን፣ የምዋሊሙ ኒዬሬሬ ፋውንዴሽን፣ የኬኔት ካውንዳ ሌጋሲ ፋውንዴሽን፣ የሲሱሉ ፋውንዴሽን ለማኅበራዊ ፍትህ፣ የፒኤልኦ ሉሙምባ ፋውንዴሽንና የሩስያው አር ቲ ሚዲያ የሁነቱ ቀዳሚ አጋር መሆናቸው ተገልጿል።
በቤተልሔም አየነው