የአድዋ ድል የኢትዮጵያዊያን የአሸናፊነት ምልክት የአፍሪካ ሀገራት የነፃነት ጭላንጭል እና የፓን አፍሪካኒዝም ካስማ ነዉ፡፡
በአፍሪካ ህብረት ምስረታ በአፍሪካዊያኑም አብሮነት ጉልህ አበርክቶ የነበራቸዉ የአፍሪካ ሀገራት መሪ ልጆችም የአድዋ ድል መታሰቢያን እየጎበኙ ነዉ፡፡
ኢትዮጵያ የትናንትን በሚዘክር ዘመኑንም በዋጀ መልኩ የአድዋ ድል መታሰቢያን ገንብታ ትናንት እንዲዘከር እያደረገች ነዉ፡፡
በጉብኝቱ የኩዋሜ ንኩርማ፣ የፓትሪስ ሉሙምባ እና መሰል የፓን አፍሪካኒዝም እና የአፍሪካ ህብረት መስራች ልጆች ተገኝተዋል፡፡
በተመስገን ይመር