የሰላም መንገድ ሁሌም ሁሉንም አሸናፊ ያደርጋል! – የሰላም ሚኒስቴር

You are currently viewing የሰላም መንገድ ሁሌም ሁሉንም አሸናፊ ያደርጋል! – የሰላም ሚኒስቴር

AMN ህዳር 26/2018 ዓ.ም

የሰላም መንገድ ሁሌም ሁሉንም አሸናፊ ያደርጋል ሲል የሰላም ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታዉቋል፡፡

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

መንግስት ለገጠሙን ችግሮች ውይይትና ንግግርን ብቸኛ አማራጭ መንገድ መሆናቸውንና ለዚህም ቁርጠኛ መሆኑን በተደጋጋሚ አሳይቷል።

ቀድሞ የሀይል አማራጭን ተጠቅመው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች ይህንን የሰላም አማራጭ በመምረጥ ወደ ሰላማዊ መንገድ ሲመጡ መንግስት ከግማሽ ርቀት በላይ በመሄድ በመቀበል ቁርጠኝነቱንም አሳይቷል። ይህ መንገድ በሀገራችን የሰላም ፣ የፍትሀዊና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ስርዓትን ለመገንባት የሚያስችል ብቸኛው አማራጭ መሆኑንም መንግስት ያምናል።

በዚህ አጠቃላይ መነሻ በአማራ ክልል ቀድሞ የሀይል አማራጭን ተጠቅመው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት የሀይል አማራጭ ለህዝባችን ሰላምና ለሀገራችን ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት ፋይዳ እንደሌለው በማመን ወደ ሰላማዊ መንገድ በመምጣት ድፍረት ያለው ውሳኔ አድርገዋል። ይህ የሰላም አማራጭ ሁላችንንም አሸናፊ ስለሚያደርግ ሚኒስቴር መ/ቤታችን ለአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት እና ለአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት( አፋሕድ) ለወሰዱት ቆራጥ እርምጃ ያለውን አድናቆት በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ ይወዳል።

በሌላ በኩል አሁንም ቢሆን የትኛውም ጥያቄ ያለው አካል ለጥያቄው መልስ ለማግኘት ብቸኛ መፍትሄው ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርገውን መነጋገርና መወያየትን መሠረት ያደረገ የሰላም መንገድ መሆኑን በማመን ኋላ ቀር የሆነውን የሀይል አማራጭ በመጠቀም የሚንቀሳቀሱ አካላት ተመሳሳይ የሰላም መንገድን እንዲመርጡ ሚኒስቴር መ/ቤታችን ጥሪ ያቀርባል ።

የሰላም ሚኒስቴር

ህዳር 26/2018

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review