ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጠቃሚነቷን ማረጋጋጥ ለሀገራዊ ደህንነቷ ወሳኝነት አለው፡፡
ሀገሪቷ የባህር በር አልባ ሀገር ሆና በቆየችባቸው ጊዜያት ውስጥ ለወደብ ኪራይ ከምታጣው ረብጣ ገንዘብ ባለፈ ሀገራዊ ደህንነቷን ለስጋት በሚያጋልጥ መልኩ የሚገቡ ንብረቶቿን የማስቆጠር የማስፈተሽ እንዲሁም ላልተፈለገ ጊዜ መባከን ዳርጓታል፡፡
ይሁን እንጂ በቀደሙት ጊዜያት ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በህግ እና በተፈጥሮአዊ የሉዋላዊነቷ ወሰን የሆነው የባህር በር የማግኘት ጥያቄ አይነኬ ጉዳይ ሆኖ ሲታለፍ ቆይቷል።
ዛሬ ያጊዜ አብቅቶ መንግስት የሀገሪቱን የባህር በር ጥያቄ ለመመለስ ሁሉንም አማራጭ መከተል ይገባል የሚል አቋም ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ነው።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ህግ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑትን ጌታሁን አለማየሁን ዶ/ር ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳብራሩት የባህር በር የማግኘት ጉዳይ የባሕር ጉዳይ ህግ ላይ ኢትዮጵያ የፈረመች ቢሆንም ያጸደቀችው አለመሆኑን ገልፀዋል፡፡
በምስራቅ አፍሪካ አከባቢ ያሉ ሌሎች ሀገራትም የፈረሙት ግን አባል ያልሆኑበት ህግ መሆኑን ገልጸዋል ።
ይህን ህግ በሁለት መልኩ ማየት እንደሚቻል ገልፀው፤ በባህር ህግ ውስጥ የተካቱት ሀገራት አባል ቢሆኑም ባይሆኑም ለሁሉም ሀገራት የሚሰራ ድንጋጌዎችን ይዟል።
ድንጋጌው ውስጥ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የባሕር በር እንዲያገኙ መብት ይሰጣል።
በተለይ ከአንቀጽ 125 እስከ 132 ያሉት ድንጋጌዎች ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት ብሎም ተጠቃሚ ለመሆን አንዱ የሚረዳት ህግ መሆኑን ገለፀዋል።
ኢትዮጵያ የሊግኦፍኔሽን፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት፣ የኢጋድ መስራች ነች ያሉት የዓለም አቀፍ የህግ ምሁሩ፤ የሌሎች አለም ዓቀፍም ሆነ አህጉራዊ ተቋማት ውስጥ ቀንደኛ ተሳታፊ ስለሆነች በዚህ መልኩ የባህር በር ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡
የባህር በር የተዘጋባቸው ሀገራት የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊ ቅንጅት ማዕቀፍ ተጠቅማ አዲስ ስምምነት እንዲመጣ ማድረግ እንደምትችል ገልጸዋል፡፡
በሰጥቶ መቀበል መርህ የምትመራው ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላትን ቅርርብ በመጠቀም በሰላማዊ መንገድ ጥያቄዋን መመለስ የምትችልበትን መንገድ ሰፊ ስለመሆኑም አመላክተዋል፡፡
በፍሬሕይወት ብርሃ