ለሶስተኛ ዙር “የመደመር መንግስታት እይታ ለዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ቃል ስልጠና ሲወሰዱ የቆዩ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች እና አባላት በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው
የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ባለፉት ቀናት ስልጠና ሲወስዱ መቆየታቸው ይታወሳል።
ከስልጠናው በኋላም በአዲስ አበባ በቅርብ አመታት የተሰሩ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።
አመራሮቹ ጉብኝታቸውን በአራዳ ፓርክ የጀመሩ ሲሆን የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በመሀመድኑር አሊ